ወደ ኢትዮጵያ ለሚያደርጉት ጥሪ ምርጡን ፓኬጅ ይምረጡ
በደቂቃ ከ10 ሳንቲም ጀምሮ ወደ ኢትዮጵያ ሞባይል እና መደበኛ ስልክ ቁጥሮች ይደውሉ። ተመኑ ዝቅተኛ ቢሆንም የእርስዎ ከወዳጅ ዘመድዎ ጋር መገናኘት ለእኛ ትልቅ ዋጋ አለው።
ቅርብ እና የተያያዘ
ሁልጊዜም ግንኙነትዎን ለማስቀጠል እና ለማደስ ለሚያደርጓቸው አጫጭር ጥሪዎች የሚስማማ፡፡
በጥልቀት ይወያዩ
ለረጅም ውይይቶች እና ጊዜ ለሚወስዱ ጨዋታዎች በቂ ጊዜ ይኑርዎት፡፡
ከወዳጅ ዘመድዎ ጋር ሁልጊዜ አብረው የይሁኑ
ልክ አገር ቤት እንዳሉ ሆነው በነጻነት ይደውሉ፣ ደጋግመው ይደውሉ — አብረዋቸው ይሁኑ፡፡
ethioCallን ልዩ የሚያደርገው ምንድን ነው?
ethioCall ከተለመዱት የመገናኛ መንገዶች — መደበኛ የጥሪ መተግበሪያዎች እና የሞባይል ሮሚንግ (— በምን እንደሚለይ እና ቤተሰቦች ለምን እኛን እንደሚመርጡ ይመልከቱ።
አይ፣ ቤተሰብዎ በዓለም አቀፍ ተመን ወደ እርስዎ የውጭ ሀገር ቁጥር መደወል አለባቸው
ብዙ ጊዜ የማይታወቁ ወይም የዘፈቀደ ቁጥሮች ሆነው ይታያሉ
አዎ፣ ባደወሉ ቁጥር ቤተሰብዎ ሴቭ ሊያደርጉት እና ሊያውቁት የሚችሉት ቁጥር
አዎ፣ ነገር ግን ጥሪዎችን ለመቀበል ብቻ ተጨማሪ ክፍያ ይደረስብዎታል
አብዛኛውን ጊዜ ወጪ ጥሪዎች ብቻ ናቸው
አዎ፣ ልክ እንደ ሀገር ውስጥ ስልክ ቤተሰብዎ በማንኛውም ጊዜ ተመልሰው ሊደውሉልዎ ይችላሉ
በጣም ከፍተኛ፣ አብዛኛውን ጊዜ በቀን ከ $1–3/ደቂቃ ሲደመር ተጨማሪ ክፍያዎች
አብዛኛውን ጊዜ በደቂቃ ከ 20 ሣንቲም በላይ
በደቂቃ ከ 10 ሣንቲም ጀምሮ
ወደ ኢትዮጵያ የሚደረጉ የሁለትዮሽ ጥሪዎች በዝቅተኛ ተመን
ወደ ኢትዮጵያ የሚደረጉ ጥሪዎች በደቂቃ ከ 10 ሣንቲም ይጀምራሉ። በልዩ አጋጣሚዎች ብቻ ድምፅዎን የሚያሰሙ ሳይሆኑ የዕለት ተዕለት ሕይወታቸው አካል ይሁኑ። ያለምንም የተጋነነ የዓለም አቀፍ ተመን፣ ድብቅ ክፍያ ከእርስዎ የሚጠበቀው ከሚወዷቸው ሰዎች ጋር ለማሳለፍ የሚፈልጉት ጊዜ ብቻ ነው፡፡
ልክ እንደ አገር ቤት የስልጥ ጥሪ ጥራት ያለው ግልጽ ድምፅ
እያንዳንዱ የሚናገሩትቃል በተናገሩበት ቅጽበት ወዲያውኑ ይደርሳል፡፡ ምንም ዓይነት የማስተጋባት ወይም የመቆራረጥ ችግር አይገጥምዎትም፡፡ ከእርስዎ የሚፈለገው የሚጠቀሙት አስተማማኝ የሞባይል ዳታ ወይም የዋይፋይ ኢንተርኔት ብቻ ነው፡፡ የኢንተርኔት ቅድመ ሁኔታዎችን በተመለከተ ዝርዝር መረጃ ከዚህ በታች ባለው መመሪያችን ማግኘት ይችላሉ፡፡
ቤተሰብዎ ተመልሰው ሊደውሉልዎ የሚችሉበት የራስዎ የኢትዮጵያ ቁጥር ይኑርዎ፡፡
ቤተሰብዎ እርስዎ መጀመሪያ እስኪደውሉ መጠበቅ አያስፈልጋቸውም። ልክ እንደ አገር ቤት ሁሉ ስልክ ቁጥርዎን ፈልገው በቀጥታ በመደወል ለአደጋ ጊዜ ወይም ለዕለት ተዕለት ወሬዎች ሊያገኙዎት ይችላሉ።
ቤተሰቦች በethioCall የሚተማመኑበት ምክንያት
በኢትዮ ቴሌኮም የተደገፈ
ethioCall የሚሰራው በራሱ በኢትዮ ቴሌኮም ኔትወርክ ነው — ቤተሰብዎ ቀድመው በሚያምኑት እና በሚተመኑበት። በሁለቱም በኩል ተመሳሳይ አስተማማኝ ግንኙነት።
እውነተኛ እገዛ፣ ከእውነተኛ ሰዎች
በእያንዳንዱ ግንኙነት በስተጀርባ እውነተኛ ቡድን አለ። አውቶሜትድ ቦት ሳንጠቀም በየትኛውም መንገድ ቢያገኙን ፣ እርስዎን ለመርዳት የተዘጋጀ ሰው ያገኛሉ፡፡
የተጠበቀ እና ደህንነቱ የተረጋገጠ
የኢንዱስትሪውን ደረጃ የጠበቀ የደህንነት ስርዓት (ኢንክሪፕሽን) እያንዳንዱን ጥሪ እና ውይይት ይጠብቃል፣ ስለዚህ የቤተሰብዎ ወሬ ሚስጥራዊነቱ የተጠበቀ ነው — ከመጀመሪያው ጥሪ እስከ መጨረሻው ስንብት።
ምንም የተሸሸገ (ድብቅ) ክፍያ የለም
የሚያዩት ተመን የሚከፍሉት ተመን ነው — ምንም ዓይነት ያልተጠበቀ ክፍያ የለም፣ ምንም ዓይነት የተሸሸገ ተጨማሪ ክፍያ የለም፣ ሁልጊዜም ቀላል እና ግልጽ አሰራር ብቻ።
ተደጋጋሚ ጥያቄዎች
ለጥሪዎች ኢንተርኔት ያስፈልገኛል?
አዎ ethioCall ጥሪዎችን ለማድረግ አስተማማኝ የኢንተርኔት ግንኙነት ያስፈልገዋል። መተግበሪያው በዋይፋይ ወይም በሞባይል ዳታ ይሰራል።
የራሴ የኢትዮጵያ ስልክ ቁጥር ያገኛል?
አዎ። ethioCall እውነተኛ የኢትዮጵያ ቁጥር ይሰጥዎታል። ወዳጆችዎ ከሞባይላቸው ወይም ከቋሚ ስልካቸው በማንኛውም ጊዜ ሊደውሉልዎ ይችላሉ፣ እና ቁጥርዎን ያያሉ — የማይታወቅ ረጅም ቁጥር አይደለም።
ጥሪዎችን ለማድረግ የኢትዮጵያ ሲም ካርድ ያስፈልገኛልን?
አይ። መተግበሪያው ሙሉ በሙሉ በኢንተርኔት ይሰራል። ለመመዝገብ የሚሰራ የሞባይል ቁጥር እና ወደ ኢትዮጵያ መደወል ለመጀመር የዳታ ግንኙነት ብቻ ነው የሚያስፈልግዎት።
ከየትኞቹ ሀገራት ወደ ኢትዮጵያ መደወል እችላለሁ?
ethioCall በአሁኑ ጊዜ በአሜሪካ፣ ካናዳ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ እስራኤል፣ የመን፣ ኬንያ፣ ዩናይትድ ኪንግደም፣ ጀርመን፣ ጣሊያን፣ ህንድ፣ ሩዋንዳ እና ሶማሊያ ይገኛል። ወደ ተጨማሪ አገሮች ለመስፋፋት በቀጣይነት እየሠራን ነው፣ አዳዲስ ሀገራትም በቅርቡ ይጨመራሉ።
በኢትዮጵያ ያለ ደንበኛ ሊደውልልኝ ይችላል?
አዎ። የእርስዎን የ ethioCall የኢትዮጵያ ቁጥር በመጠቀም በኢትዮጵያ ያሉ ደንበኞች በቀጥታ ሊደውሉልዎ ይችላሉ።
የኢትዮጵያ ቁጥሬን ለረጅም ጊዜ ማቆየት እችላለሁን?
የኢትዮጵያ ስልክ ቁጥርዎ ጥቅልዎ ከሚያበቃ በኋላ ለ30 ቀናት ንቁ ሆኖ ይቆያል፣ አዲስ ጥቅል ለመግዛት በቂ ጊዜ እንዲኖርዎት። በዚህ ጊዜ ውስጥ ካደሱት ተመሳሳይ ስልክ ቁጥርዎን ይቀጥላሉ።
ፓኬጁ ለምን ያህል ጊዜ ያገለግላል?
የ1 ቀን፣ የ7 ቀን እና የ15 ቀን ጥቅሎችን እናቀርባለን። ወደ ኢትዮጵያ የሚደውሉበትን ድግግሞሽ የሚስማማ ጥቅል ይምረጡ።
አስተማማኝ የጥሪ ጥራት ማግኘት እችላለሁ?
የጥሪው ጥራት ከኢንተርኔት ግንኙነትዎ ጋር የተያያዘ ነው። በአስተማማኝ ዋይፋይ ወይም 4G/5G የሞባይል ዳታ ላይ ጥሪዎች ግልጽ እና ያልተቋረጡ ናቸው — ምንም አስተጋባ የለም፣ ምንም መዘግየት የለም።
መረጃዬ ደህንነቱ የተጠበቀ ነውን?
የመለያዎ እና የግል መረጃዎ የኢንዱስትሪውን ደረጃ የጠበቀ የደህንነት ስርዓት በመጠቀም የተጠበቀ ነው። መረጃዎን ከቶም ለሌላ ወገን አናካፍልም ወይም አንሸጥም።
አካውንቴን እስከወዲያኛው እንዴት ማጥፋት እችላለሁ?
ማጥፋት የሚከናወነው ሙሉ በሙሉ በመተግበሪያው ውስጥ በመለያው ባለቤት ነው። ጥያቄውን ለማቅረብ በመለያዎ መግባት አለብዎት።
መለያዎን እንዴት ማጥፋት እንደሚቻል፡ ethioCallን ይክፈቱ → ወደ Account ይሂዱ → Settingsን ይክፈቱ → User Infoን ይጫኑ → Delete Accountን ይምረጡ → Delete Forever በማለት ያረጋግጡ
ሲያጠፉ የሚከተሉት ይከናወናሉ፡
· መለያዎ መልሰው ማግኘት በማይችሉበት ሁኔታ በዘላቂነት ይሰረዛል
· ከመለያው ጋር የተያያዙ ሁሉም የግል መረጃዎች ይወገዳሉ
· የጥሪ ታሪክ እና እንቅስቃሴዎች ይሰረዛሉ
· የእርስዎ ቁጥር፣ የተገዙ ፓኬጆች እና የክፍያ ታሪክ በአንድ ሰዓት ውስጥ ይወገዳሉ
· ሂደቱ አንዴ ከተረጋገጠ በኋላ ወደ ነበረበት መመለስ አይቻልም